ሕዝብን በማወናበድ ከእውነታው ማምለጥ ከቶ አይቻልም! ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ

ህዳር 16/2009   ሕዝብን በማወናበድ ከእውነታው ማምለጥ ከቶ አይቻልም!

The Split of Arbegnoch Ginbar and Ginbot 7 – Interview with EPPF/Arbegnnoch Ginbar (AG7 member party) Officials, 30 Sep 2016

(Mereja) — በሀሃገራችን ኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ ያለውን የነጻነት ችቦ እየነደደ ባለበት በዚህ ወቅት የግንቦት 7 እና መሪዎቻቸው የሕዝብን ትግል የራሳቸው በማስመሰል በሌለውና በፈረሰው የአርበኞች ግንቦት 7 ስም የሚደረገው የስም ንግድና ዘመቻቸው ሕዝብን እያወናበዱት ይገኛል

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ከነሓሴ 3/2008 ዓ.ም ጀምሮ በተደጋጋሚ ባወጣው መግለጫ  ውህደቱ ያለሰመረና መፍረሱን ገልጧል። ከውህደቱ በፊት በተለያዩ ጊዜያት የግቦት ሰባት አመራሮችና አባላት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የሚባል የለም፣ከየቦታው የተሰባሰቡ ሽፍቶች ናቸው፣ የተማረ የሰው ሃይልና ብቃት የላቸውም፣ እንደውም በጨረሻ በራሳቸው ጊዜና ሰዓት ይጠፋሉ በማለት በሚዲያቸውና በየፓልቶኩ እየቀረቡና በስማ በለዎቻቸው ሲሳለቁ አልሰማንም እንደማትሉን ተስፋ እናደርጋለን። እውነት የሽፍቶችና አላዋቂዎች ስብስብ ከሆንን የግንቦት ሰባት ድርጅትና አመራሮቹ  ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ላይ የሙጥኝ ያሉበት ምክናየት ምንድን ነው ?  እንደ ግንቦት ሰባት አባባል ሰራዊት ካለውና በየጊዜው የሚያስመርቀው ሃይል ከምን ደረሰ? በአርበኞች ግንቦት ሰባት የሚሰበሰበው ገንዘብ ለመሪዎቻቸውና አፈቀላጤ አባሎቻቸው የመንሸራሸሪያና ደሞዝ ከመሆን ባሻገር ለሰራዊቱ ምን ደረሰው? ምንስ ተደረገለት? እንደ አንድ ሃገር ዜጋና ተቆርቋሪ ቆም ብላችሁ ለትመረምሩና ልታስቡበት የሚገባ ቀላል የሂሳብ ስራ ነው። ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር በርካታ አባሎቻችን በተለያዩ ጊዜያት  መሰዋታቸው ይታወቃል ይሑኝ እንጂ አንድም ጊዜ ቢሆን የተሰዉትን አርበኞች ፎቶ አቅርበን ገንዘብ አዋጡ ያልንበት ጊዜ ግን የለም ወደፊትም አይኖርም። አሁን በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ወንድማችን ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በወያኔ ተከቦ በርካታ ወያኔዎችን መግደሉና በመጨረሻ እራሱን መሰዋቱ ይነገራል። ከሆነ ሻለቃው  የገደላቸው ወያኔዎች ሬሳ ካካባቢው የት ገባ? በወያኔ ተከብቦ ከነበረ ፎቶ ግራፍ ያነሳው አካል ማነው? እጅ አልሰጥም ብሎ እራሱን ሲያጠፋ ማን አየው? ለግንቦት ሰባቶች ፍንጭ ለመስጠት ያህል ዜናውን ቢያሻሽሉትና “ፎቶውን ያገኘነው ከወያኔ የውስጥ አባላችን ነው “ ካላችሁ የሻለቃ መሳፍንት አስከሬን መጨረሻ ምን እንደሆነ መግለጽ ግድ ይላችኋል።

የተመለከትነው የሻለቃ መሳፍንት አስከሪን እንደሚያሳየው በተባለው ጠዋት እራሱን ያጠፋ ሰው ሳይሆን ከሞተ ከ3 እስከ 5 ቀን የቆየ አስከሬን እንደሆነ የሰውነቱ ማበጥና ተስተካክሎ ለፎቶ አስቀምጠው እንዳነሱት ያስታውቃል። ግን ይህ ሁሉ ወዥንብር ለምን አስፈለገ? ግንቦት ሰባት ሻለቃውን ከሰራዊቱ ጋር ጋር ቆሞ ለጉዞ እንደተዘጋጀና  ለፕሮፖጋንዳ ያሰየን የቪዲዮ ስዕል ላይ የለበሰው የወታደራዊ ልብስ ወልቆ በሽርጥና በወዳደቁ ጨርቆች ተሸፍኖ አይተናል ይሁንና ከቀኝ እጁ ላይ የማይለየው የኢትዮጵያ አርንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ጌጥ የት ገባ ? የሚሉት ጥያቂዎች በሁላችሁም አእምሮ ይመላለሳል ብለን እንገምታለን ። የወያኔ ተከታይ ጉጅሌ ወታደር በባህሪ የተዋጉትን አርበኞች ሞተውም ካገኘ ሬሳቸውን በየከተማው እያዞረ ያሳያል፣ ይሰቅላል፣ አልያም ከዚህ ቀደም እንዳያችሁት አጥር ላይ ሰቅሎ ለህዝብ ያሳያል። ይህ ካልሆነ ደግሞ አስከሬኑን ወደ አካባቢው ፖሊስ ጣቢያ ይወስዱታል ህዝብም እንዲያየው ይደረጋል። ይህን አይነት አጋጣሚዎች ለበርካታ አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና ሌሎች የነጻነት ታጋዮች ላይ በተደጋጋሚ ደርሷል ይታወቃልም ። ታዲያ ይሄ እንዴት ተለየ ? ፈጣን መልስ የሻል። ሰለሆነም በዚህ ሻለቃ ወንድማችን ላይ የደረሰው አሟሟት እንዲት እንደሆነና በምን ምክናየት ሊሞት እንደቻለና ፎቶ ግራፍ ያነሳው ክፍል ማን እንደሆነ የመሳሰሉት በርካታ ጥያቄዎች ሚስጥር ሆነው እንደማይቀሩ ሊታወቅ ይገባል ።  በዚህ በያዝነው ሳምንት ብቻ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአንገረብ፣በሳንጃና ሰሮቃ ያሳየው ፊልሚያ እጅግ የሚያኮራና የትጥቅ ትግል መሳሪያቸውን ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት ሃይላት ጋር በጋራ በተጠቀሱት ስፍራዎች ያሳየው ተጋድሎ በበርካታ ወራት ከተገኙት ድሎች ዋነኛው ነው።

አንድነት ሃይል ነው!!                                                                                     ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር

No comments yet.

Leave a Reply

Designed and Developed by NextGen IT Solutions