ቆንጨራ ያላነሳ ሃይማኖት አልነበረም!

ቆንጨራ ያላነሳ ሃይማኖት አልነበረም!

ዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ, PH.D.*

ክፍል 1


አብዛኛውን ጊዜ የኅይማኖት ምንጮች ሁሉ በጥልቀት አንብበው ‹የተረዱ› ሰዎች (1) ለብዝሃ ኅይማኖት እውቅና ይሰጣሉ (2) ሁሉም ሃይማኖቶች ሰላማዊ ግንኙነት እንድፈጥሩና በሰላም አብሮ እንድኖሩ ያበረታተሉ (3) ጽንፈኝነትን ይከላከላሉ ወዘተ። ጀርመናዊው ምሁር ማክስ ሚለር ትክክል ነበር ማለት ነው! ሚለር ‹‹በእኛ አይን የጐረቤታችን ዶሮ ዝይ ናት›› ከተሰኘ ኋላ-ቀር አመለካከት ለመላቀቅ፣ አንድ ኅይማኖት ብቻ ማወቅ በቂ እንዳልሆነ ያሰምርበታል—he who knows one religion knows none! ስለ ኅይማኖት ምንነት የተሻለ ግንዛቤ እንድኖረን ከተፈለገ፣ በተቻለ መጠን የራስን ብቻ ሳይሆን፣ የሌሎችንም ኅይማኖት አጀማመርና ታሪክ (አመጣጥ) በጥልቀትና በስፋት ማጥናት ያስፈልጋል ማለት ነው።

ይሁን እንጅ፣ በዓለማችን ላይ አንድ ወጥ ኅይማኖት ብቻ እንድሰፍን ተግተው የሚሠሩ (ጽንፈኛ አመለካከት ያላቸው) ግለሰቦች መኖራቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። እነኝህ ሰዎች የለሎችን የግል እምነትና ነፃነት የሚደፍሩ ሲሆን፣ ፍላጐታቸውም የራሳቸውን እምነት አሳድገው፣ የለሎችን ጨርሰው ለመደምሰስ ነው። ይህ ዘግናኝ እኩይ ድርጊት በዋናነት የሚመነጨው ከድንቁርና ነው። ስለሚንከተለው እምነት ምንነት በቂ ግንዛቤ ሳይኖረን፣ ‹የሃይማኖት እኩልነትን አንቀበልም› ብሎ ክላሽ ማንጣጣት ድንቁርና ካልሆነ በስተቀር ምንም ሊሆን አይችልም። ‹‹አድስ እረኛ ከብት አያስተኛ›› ነው ነገሩ!

‹‹የለሎች ሃማኖት ጨርሰው መደምሰስ›› የሚል የድንጋይ ዘመን ፍልስፍና፣ በዘመኑ ዓለም ውስጥ (in contemporary world) ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። የሌላውን ሃይማኖት እየናቁ የራስን ማክበር በሳልነት አይደለም። ማንኛውም ሰው ነፃ-ፍቃዱን ተጠቅሞ የፈለገውን ሃይማኖት፤ እምነት እና አስተሳሰብ የመከተል ወይም የመያዝ ተፈጥሯዊ መብት አለው። ቅዱሳት መጽሐፍትም ይህንን እውነታ ያረጋግጣሉ፤ ‹‹የፈለገ ይመን የፈለገ ይካድ›› (አል-ከህፍ፤ 29) ‹‹በፊታችው ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ›› (ኦሪት ዘዳ. 30፡ 19) በሀገራችን ኢትዮጵያ፣ የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 27 ማንም ሰው ያመነበትንና ህልናው የፈቀደውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመከተል ተፈጥሯዊ መብት እንዳለው በግልጽ ያስቀምጣል። ስለዝህ፣ በዝ ረገድ ሕገ-ምንግስቱ የሚለንን ማክበር የግድ ይላል!

ስለዝህ፣ ‹‹የለሎች ሃማኖት ጨርሰው መደምሰስ›› የሚለው ሰይጣናዊ ፍልስፍና የሚያቀነቅኑ ሰዎች ይህንን መብት ከየት እንዳገኙ ለማወቅ እስካሁን ያደረኩት ጥረት አልተሳካልኝም። አቤ ጉበኛም እንድ ሲል ይጠይቃል፡- ‹‹እግዝአብሔር አንዱን ሐይማኖት ብቻ የሚወድ ቢሆን የሚወደውን የዓለም ሃይማኖት አድርጎ የቀሩትን አያጠፈቸውም? እሱ ካላጠፋቸውስ ማን ሊያጠፋቸው ይችላል? ከሱ የበለጠ እሱ የሚወደውን ነገር እናውቃለን? እንግድህ እግዝአብሔር በዕውቀቱ የሚያኖራቸውን ልዩ ልዩ ሃይማኖት የያዙ ሰዎች በልዩነት ማየትን እንተው።›› (አቤ ጉበኛ፤ አልወለድም፣ ገጽ. 81-82) ኬንያዊው ምሁር ፕ/ር ኪሁምቡ ታይሩ የአቤን ሐሳብ በፈረንጅኛ ስያጠናክር እንድህ በማለት ነበር፡-

‹‹The question that one has to ask is, what right has anybody got of telling you that the God of your people who has preserved you all these years (otherwise you would not be there), is a false God? To say that the God of a particular people is untrue is to declare that those people are themselves not quite people. This statement is fully illustrated by the examples in history where some nations were brutally exterminated without raising much trouble in the conscience of their exterminators because the former were ‘worshippers of false Gods.’” (Kihumbu Thairu, African Civilization 1975, pp. 67-68)

ነባራዊ እውነት አንድ ብቻ መሆኑን ፈጽሞ መካድ ባንችልም፣ የሰው ልጅ ተፈጥሮ በጊዜና በቦታ የተወሰነ በመሆኑ፣ እውነታን የሚረዳበትና የሚያብራራበት መንገድ (ዘዴ) የተለያየ ሊሆን ይችላል። ሃይማኖት እስከገባኝ ድረስ፣ እያንዳንዱ ግለሰብ፣ የአንድ ሃይማኖት ተከታይ የሚሆነው በደመ-ነፍስ ተመርቶ ሳይሆን፣ ‹‹በእኔ እምነት ውስጥ በትክክል የእውነት ሙላት አለ፤ በፍጹም እኔን ሊያድነኝ የሚችለው እምነት ይኸኛው ነው፣ ሃይማኖቴን የሚከተለው ከልብ በመነጨ ፍቅርና ደስታ እንጅ፣ ማንም ሰው ስላስገደደኝ አይደለም› ብሎ ከልብ ሰላመነበት ይመስለኛል። ይህ የሚያሳየው አንድ ሰው የቤተ-እምነቱን ቀኖና በሚገባ ስለተከተለ ብቻ ጽንፈኛ ተብሎ መፈረጅ የለበትም። ምክንያቱም፣ ጽንፈኝነት የሌላውን እምነትና አስተምሮ ማጥላላት እንጅ፣ የራስን ሃይማኖት ማክበርና ቀኖናውን በጽኑነትና በታማኝነት መከተል ጋራ የተያያዘ አይደለምና።

ስለዝህ፣ አንድ ሃማኖት የተከበረና የበላይ ሌላው የተናቀና የበታች አድርጎ ማቅረብ በማንኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም። በሃይማኖት ምክንያት የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማስቀረት ከተፈለገ፣ ሃይማኖታዊ ልዩነቶቻችን ላይ ሳይሆን፣ የጋራ ሃይማኖታዊ እሰቶቻችን (ፍቅር፤ ሰላም፤ደስታ፣ ፍትሕ፣ ቅንነት፣ መልካም አሳቢነት፣ መከባበር…ወዘተ) ላይ ማተኮር የግድ ይላል። ‹‹ፍቅር መግዛት ከፈለግህ፣ ፍቅር ራሱ መክፈል ያለብህ ዋጋ ነው›› እንደሚባለው የእኛ እምነት ወይም አመለካከት እንዳይነካብን ከፈለግን፣ የሌላውን ሃይማኖት ፈጽሞ ማጥላላትና መናቅ የለብንም። በተለይ፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለፈውን ታሪክ እየነካኩ፣ የሌላውን ሃይማኖት ወይም እምነት ማጥላላት አደጋ አለው። ይህ ማለት ግን ትናንትና በሃይማኖት ምክንያት የተፈጸሙትን ስህተቶች አደበስብሰን ማለፍ አለብን ማለት አይደለም። ጥያቄው መሆን ያለበት ‹‹ከትናንትናው ታሪክ ምን እንማራለን?›› ነው! ኢሰባዊነት የተንጸባረቀባቸው አስከፍ ግጭቶች ዳግም እነዳይከሰት ከፈለግን፣ እያንዳንዳችን ካለፈው ታሪክ በመማር ለብዝሃ ኅይማኖት እውቅና መስጠት ይኖርብናል። ቆንጨራ ያላነሳ ሃይማኖት አልነበረምና፣ የታሪክ ሂሳብ እንወራረድ የሚል ግልብ አስተሳሰብ የትም አያደርሰንም! አሜን!

ምንጭ፡- ዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ፣ የኢትዮሮፒያንስ የአስተሳሰብ ቅሬ፣ ገጽ. 74-75

2 Responses to ቆንጨራ ያላነሳ ሃይማኖት አልነበረም!

 1. ፈቃደ May 11, 2017 at 11:00 pm #

  ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ከመቶ ዘመናዊ የግል አውቶሞቢሎች ለወያኔዎች በሚያዳላ አነስተኛ ግምት ስልሣው የትግሬ ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚታዩ መቶ ታላላቅ የግንባታ ሥራዎች መካከል ዘጠና አምስቱ የትግሬ ናቸው (አጠገቤ ያለ አንድ ጓደኛየ ግን መቶ በለው እያለኝ ነው) – ለምን እንዋሻለን? ከትግሬዎች ጋር ምንም ዓይነት ውድድር የለም፤ እነሱ ሁሉ በጃቸው ሁሉ በደጃቸው ነው – ያለቀረጥ ይነግዳሉ፤ ያለቫት ይነግዳሉ፤ ያለቤት ኪራይ ይነግዳሉ፤ ያለ ፍትህ ያስፈርዳሉ፤ እነሱ ገድለው ሟችን ይከሳሉ፤ እነሱ ዘርፈው በተጠቂነት ምስኪኖችን ይከስሳሉ፡፡ በጥቅሉ ኢትዮጵያና ሕዝቧ በነሱ ታግተው በስቃይ እየማቀቁ ናቸው፡፡ ስለዚህ አዲስ አበባ መቀሌ ሆናለች፡፡ የማውቃት አዲስ አበባ ወዴት ሄደች ብለህ ብትጠይቅ መልሱ በመቀሌ ተዋጠች ነው – መቀሌን ሆነች፡፡ ሀፍረተ ቢሱ ሕወሓት ይህን ሁሉ አጃኢበት እየሠራ እነኢትዮሚዲያ “ትግሬ አልተጠቀመም” ብለው ሆዳቸውን ነፍተው – ምንድን ነው እባለው አማርኛውም ጠፋኝ – አዎ፣ ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ ትንሽ አይሰቀጥጣቸውም፡፡ ክርስቶስ ለሥጋው አደላ እንደተባለው እነሱም – ሰውነት ተረስቶ የአንዲት ሀገር ዜግነት ተዘንግቶ – ለደም ቁርኝት ሲሉ ብቻ ይህን ሁሉ አዲስ አበባ ላይ ማለትም አዲሷ መቀሌ በአዲስ አበባ ከርሰ መቃብር ላይ … ዛሬ ምን ነካኝ … ፊንፊኔ ላይ … ኦ! አይደለም … ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ ይሄ ለሰማይ ለምድር የከበደ ግፍና በደል እየተሠራ እያዩ የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝ ብለው ዐይናቸውን ጭፍን፣ ጆሯቸውን ጥቅጥቅ፣ አንደበታቸውን ልጉም አድርገው ሲያበቁ እውነቱንና እውነቱን ብቻ የምንናገረውን ወገኖች በሀሰተኝነትና በጥበት በስፋት ይከሱናል፡፡ ይልቁንስ አዲስ አበባ የጠፋቻችሁ ካላችሁ አብረን እንፈልጋት፡፡ ምንም አልተናገርኩም፡፡ አዲስ አበባ ከፊንፊኔ/አዲስ አበባነት ይልቅ ለመቀሌነትና ዐድዋነት እጅግ ትቀርባለች፡፡ የስሚንቶውም በሉት የብረቱ፣ የምግቡም በሉት የመጠጡ፣ የልብሱም በሉት የመድሓኒቱ፣ የሸቀጡም በሉት የመኪና መገጣጠሚያው … ከሞላ ጎደል ሁሉም ፋብሪካና ኢንዱስትሪ የነሱ ነው፤ እኛ አሽከርነቱ ነው የተረፈን – ለዚያውም ከእስር፣ ከስደት፣ ከበረሃ ዐውሬና ከሞት ከተረፍን፡፡ ሆቴሎች፣ ሱፐርማርኬቶች፣ ባንኮችና ኢንሹራንሶች፣ የመኪና መለዋወጫ ሱቆች፣ የግንባታ ዕቃ ማምረቻና ማከፋፈያ መደብሮች፣ ዱሮ ጉራጌ የተንቀባረረባት ማርካቶ እንዳለች፣ አያት የመኖሪያ ቦታ፣ ሲኤምሲ የመኖሪያ ቦታ፣ ሰሚት የመኖሪያ ቦታ፣ ሁሉም ዐይን ዐይን የመኖሪያ ቦታ፣ቀጫጭንና አነስተኛ ንግድ፣ ወፋፍራምና ጠረንገሎ ንግድ፣ አብዛኞቹ የግል የትምህርት ተቋማት (በሁሉም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ባሉት)፣ የማዕድን ምርቶች፣ እኔና ሚስቴ ከነልጆቻችን … ምን አዘረዘረኝ … ምንስ አደከመኝ … ከፀሐይ ብርሃንና ከምንተነፍሰው አየር በስተቀር – ለነዚህም ባልቦላ ሊገጥሙ ነው ተብሎ እየተናፈሰ ነው – ሁሉም ነገርና ሁላችንም በነሱ ወለድ አገድ ተይዘናል፡፡ አዲስ አበባ በመቀሌ መተካቷን ለመገንዘብ ማታ ማታ ቡና ቤቶችን ጎብኝ ከፈለግህ፡፡ ምድረ አድርባይና አቃጣሪ – ይህ ቃል እንዴት ያስጠላል – ቆይ ልቀይረውማ – ምድረ አሽቃባጭና እወደድ ባይ – አብዛኛዎቹ የምሽት ደምበኞቹ ትግሬዎች ስለሆኑ ብቻ ትግርኛ ዘፈን አሁንም አሁንም እንዲያምቧርቅ ዲጄውን ያስገድዳል፤ ለነገሩ አብዛኛው ባለቡና ቤትና ባለዝጉብኝ ግሮሠሪ ትግሬ ነው – ሌላውማ ምን ተመችቶት? በደርግ ዘመን “ምርጥ ምርጡ ለሕጻናት” ይል የነበረው መፈክር አሁን ምርጥ ምርጡ ለትግሬ ነው – ያኔ ለመፈክር ነው – አሁን ግን በተግባር፡፡ እነሱም – ትግሮቹም – ከፍ ሲል እንደተገለጸው ሁሉም ሣይሆኑ በተለይ ባለጊዜዎቹ ቀላሎች ናቸውና በትግርኛ ዘፈን ሽቅብ እየዘለሉ የሰማይን ጣሪያ በእጃቸው ሲቧጥጡ፣ የምድርን ወለል በእግራቸው ሲደ(ል)ቁ ያድራሉ፡፡ ከአልኮሉ ጋር በተቀላቀለ የበላይነት ስካርም ጥምብዝ ብለው ሲያሽቃንጡ ለሚመለከታቸው ያሳዝናሉ፡፡ በአንድ አዳር የሚያወጡት ገንዘብ ሲታይ ደግሞ የገንዘብ ማተሚያ ማሽን ያላቸው ይመስላል፡፡ እኚህ ማይሞች አዲስ አበባን እንደሞጄሌና አልቅት ተጣብቀውባት አሣሯን እያሳዩዋት ነው፡፡ ትግሬ ስንል እንግዲህ እኛን በዘረኝነት ሊከሱን የሚቃጣቸው የዓዞ ዕንባ አንብዎቻችን – እሽ አትበሉን የሹም ዶሮዎች ነን ባዮቹ – ይህን ሁሉ የዘመዶቻቸውን ጉድ እንዳይታይ ደብቀው የጥግንግን ለውጥ እንዲመጣና አንዱ ወያኔ በሌላው እንዲተካ የሚፈልጉ የገበሎ ልጅ እንሽላሊቶች ናቸው፡፡ Basically, you cannot talk of an effect without mentioning its cause; and as a matter of fact, unless the cause is identified, you cannot find a solution to a hidden cause whose effects are profusely spread resulting in the fatal victimization of millions of people all over Ethiopia. ማንኛዋ ሴትኛ አዳሪ ትሆን “ጉንጬን ሳትነካ ሣመኝ” ብላ ለወዳጇ የተናገረችው? የትግሬ ስም አይነሳብን የሚሉ ዓለመኞች ናቸው፡፡ እናታቸው ወንዝ የወረደችባቸውን ሞልቃቃ ልጆች ያህል እንኳን አልተጎዱም እኮ፡፡የአዲስ አበባ ኮንዶምንየም ደግሞ ለአዲስ አበባ ነዋሪ ብቻ ነው የሚሰጠው ወይም መሰጠት የሚገባው፡፡ እነኚህ ወያኔዎች ግን ኮንዶምንየሙን ሁሉ የሞሉት ከትግራይ በሚመጡ ትግሬ ዘመዶቻቸው ነው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ ንግዱም ሆነ ሥራው የሚሞላው ከትግራይ ገጠርና ከተማ ቦታዎች በየቀኑ እንደግሪሣ በሚተሙ ማይማን ትግሬዎች ብቻ ነው፡፡ ያዋጁን በጆሮ፡፡ ሌላው ሌጣውን እየቀረ ነው፡፡ምኑንም ሳልናገር ደግሞ ገፆችን ያህል ወረድኩ፡፡ ቀን ይክፈለን፡፡ ለማንቻውም የቴዲን አዲስ ዘፈን እንገባበዝና ለጊዜው እንሰነባበት – እባካችሁን እነዘሀበሻና ኢካድፍ፣ እነወልቃይትና ቋጠሮ – የስንቶቻችሁን ስም አንስቼ እጨርሰዋለሁ –.

  ግምቦት ፫ ( ሦስት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና
  “ችግሩ ከአቅማችን በላይ እየሆነ ስለመጣ ያለን ብቸኛ አማራጭ ድርጅታችንን ዘግተን መሰደድ ብቻ ነው።” ሲሉ የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ብሶታቸውን በምሬት ገልጸዋል።:-

  የአዲስ አበባ ንግድና የገቢዎች ቢሮ በተጨማሪ የዋጋ ግብር ማለትም በቫት አዋጅ ስም የድርጅቱን ሠራተኞች ገንዘብ እየሰጠ በሰላይነት በማሰማራት ነጋዴዎች ላይ ምዝበራ እየፈጸመ መሆኑን ነጋዴዎች አጋለጡ።
  ነጋዴዎቹ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት የአገዛዙ ሹመኞች ነጋዴዎችን ከሕግ አግባብ ውጪ በመክሰስና የሃሰት ምስክሮችን በማቆም የነጋዴው ማህበረሰብንማሰርና ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ መቀጮ ማስስከፈል ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል።
  የንግድና ገቢዎች ቢሮ በሚልካቸው ሰላዮች አማካኝነት ምዝበራ እየተፈጸመባቸው መሆኑን የሚገልጹት ነጋዴዎቹ፤ የቢሮዎቹ ሰላዮች በየሳምንቱ ወደሥራቦታቸው እየመጡ ከአምስት ሺህ ብር በላይ ጉቦ እየተቀበሉዋቸው መሆኑን በምሬት ተናግረዋል።
  የቢሮዎቹ ሰላዮች፤የተጠየቁትን ጉቦ የመክፈል አቅሙ የሌላቸውን ነጋዴዎች የንግድ ድርጅቶች እስከ ማዘጋት መድረሳቸውም ተመልክቷል።
  ከዚህም በላይ ንግድና ገቢዎች ቢሮ ከሰሞኑ በንግድ ቤቶች ላይ የቁርጥ የቀን ገቢ ግምት ማውጣት የሚል ዘመቻ መጀመሩን የገለጹት ነጋዴዎች፤ ገማቾቹ፤ንግድ ቤቶቹ በሳምንትም የማያስገቡትን ገቢ በቀን ሽያጭ እየገመቱ ድርጅታቸውን እንዲዘጉ እያስገደዷቸው መሆኑን ይናገራሉ።
  ግምቱ እንዲቀንስላቸውና ድርጅቶቻቸው ከመዘጋት እንዲተርፉ ከፈለጉ፤ ለሶስትና አራት ገማቾች የዓመት ትርፋቸውን የሚያክል ጉቦ በጉዳይ አስፈጻሚደላሎቻቸው በኩል እንደሚጠየቁ ነጋዴዎቹ አጋልጠዋል።
  ነጋዴዎች በመጨረሻም፦ ”በአንድ በኩል በቫት፣ በሌላ በኩል በቀን ሺያጭ ግምት እንዲህ የሚያሰቃዩን ተማረን የንግድ ፈቃዳችንን እንድናስረክብ በማሰብነው። ፈቃዳችንንና የንግድ ቤቱን እንድናስረክብ የተፈለገውም፤ ለገዥው ፓርቲ ሰዎች ለመስጠት ታስቦ ነው። ችግሩ ከአቅማችን በላይ እየሆነ ስለመጣ ያለን ብቸኛ አማራጭ ድርጅታችንን ዘግተን መሰደድ ብቻ ነው።” ሲሉ ብሶታቸውን በምሬት ገልጸዋል።

Leave a Reply

Designed and Developed by NextGen IT Solutions