አፈ-ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ራሳቸውን ከኃላፊነት አነሱ!

The Speaker, Abadula Gemeda, of the House of Peoples’ Representatives (HoPR) resigns a day after Brigadier General Melaku Shiferaw who served with the military intelligence of the regime’s defected in the USA.

ሰኞ መስከረም 28/2010 ዓ.ም 5ኛው ዙር የ3ኛ አመት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ይጀመራል። ይህን አስመልክቶ የሪፖርተር ጋዜጣ ሁለት ጥያቄዎች አቅርቦልኝ ነበር። የመጀመሪያው ባለፉት ሁለት አመታት በሀገራችን ከነበረው አጠቃላይ ፖለቲካዊ ሁኔታ አንፃር ሲታይ “የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሚወክሉትን ሕዝብ በሚገባ እያገለገሉት ነው ወይ?” የሚል ነበር። ይህ ጥያቄ ምክር ቤቱ በሕገ መንግስቱ ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት አንፃር መታየት አለበት። በዚህ መሰረት የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቼ ነበር፡-

“ባለፉት ሁለት አመታት በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ተቃውሞና አድማ ተካሂዷል። ዜጎች ለተቃውሞ አደባባይ የሚወጡት እና የሥራ አድማ የሚጠሩት፤ አንደኛ፡- በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 30ና 42 ላይ በግልፅ የተደነገገ ዴሞክራሲያዊ መብት ስለሆነ ነው፣ ሁለተኛ፡- ዜጎች የነፃነት፥ እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ስላላቸው ነው። ነገር ግን፣ ዜጎች ለተቃውሞ አደባባይ ሲወጡ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ የብዙዎች ሕይወትና ንብረት ጠፍቷል። ይህ ሁሉ የሆነው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 55 መሰረት የተሰጣቸውን ስልጣንና ኃላፊነት በአግባቡ ባለመወጣታቸው ነው።”

የስሞኑ ታላላቅ ዜናዎች ፦ የጠቅላይ ሚንስቴር ኅይሌማርያም ደሣለኝ ኘሮቶኮል ኃላፊ የነበሩ አቶ ባዬ ታደስ ተፈሪ እንድሁም በወታደራዊ ደህንነት ቢሮ ሜ/ጀኔራል መላኩ ሺፈራው ጥሩነህ የወያኔን ስርአት ከድተው በአሜርካ ጥገኝነት መጠየቅ ፣ ከአገር ቤት ሦስት ጀኔራሎች ሁለቱ በትግራይ ሽሬ አካባብ የተወለዱ አንዱ ለግዜው ብሔሩ ያልተለየ እርስ በርስ መገዳደላቸው የታወቀበት ሣምንት ሲሆን ይህ የምያሳየን የወያኔ ስርአት በስብስው ለመውደቅያው ጫፊ ላይ መድረሱን ነው። ይህ ስው በላ የአናሣ ሽፊታ ቡድን መንግስት መውደቅያውን እንኳ ላለማሣመር ጭቁን ሕዝቦች እርስ በርስ ለማበላላት ሴራውን ገፊቶበት እነሆ ብጠውን አብዲ እሌ የምባል ተራ የጉልበት ሠራተኛ ከመንገድ አንስተው የማይገባውን ስልጣን አስጨብጠውት ዛሬ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ጦርነት ያሣውጃል።ማን እንደምጎዳበት ጊዜ ያሣየናል።ደግነቱ ኦሮሞ አናሣ አይደለም !

ሁለተኛው የሪፖርተር ጥያቄ ደግሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያሉበትን ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ “በቀጣይ ምን መደረግ አለበት?” የሚል ነው። ለዚህ ጥያቄ የሰጠሁት ምላሽ በጣም አጭርና ግልፅ ሲሆን፣ እሱም “የምክር ቤቱ አባላት ለኢህአዴግ መንግስት ሳይሆን ለሕገ-መንግስቱ፣ ለሕዝቡና ለሕሊናቸው ተገዢ በመሆን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ይወጡ!” የሚል ነበር።

አዎ… እያንዳንዱ የሕዝብ ተወካይ ያለው ምርጫ የመሆንና ያለመሆን ምርጫ ነው። ለፌደራሉ መንግስት ተገዢና አገልጋይ መሆን ወይም ለሕገ-መንግስቱ፣ ለሕዝቡና ለሕሊናው ተገዢ መሆን። የፌደራሉ መንግስት በአንድ ወገን፣ ሕገ-መንግስቱና ሕዝቡ በሌላ ወገን ሆነው ተለያይተዋል። ስለዚህ አንድ የምክር ቤት አባል ለፌደራሉ መንግስት እና ለሕገ መንግስቱና ለሕዝቡ እኩል ተገዢና አገልጋይ ሊሆን አይችልም።

ትላንት እኩለ ሌሊት ላይ “የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ራሳቸውን ከኃላፊነት አንሱ” የሚል ጭምጭምታ ስሰማ ብዙም አልገረመኝም። ምክንያቱም በሀገራችን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር አፈ-ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ሆኑ ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ያላቸው ምርጫ አንድና አንድ ነው። እሱም ኃላፊነታቸውን በፍቃዳቸው በመልቀቅ ራሳቸውን ከፌደራል መንግስቱ ማግለል ነው።

አፈ-ጉባዔ አባዱላ ገመዳ በራሳቸው ፍቃድ ስልጣናቸውን የለቀቁበት ምክንያት በዋናነት በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል መካከል በተፈጠረው ግጭት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጣልቃ-ገብነትን በመቃወም እንደሆነ ተሰምቷል። በእርግጥ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ በምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ነዋሪዎች ላይ እየፈፀመ ያለው ጥቃት በአስቸኳይ መቆም ያለበትና ይህ እንዲሆን የፈቀዱ የክልሉ መንግስት ኃላፊዎች በሕግ ተጠያቂ መሆን አለባቸው። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሁኔታውን ለመቆጣጠርና የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ጥረት እያደረገ አይደለም። በመሆኑም የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በማንአለብኝነት ከ200ሺህ በላይ ዘጎችን ሲያፈናቅል ከ200 በላይ ደግሞ ገድሏል። በዚህም እንደ ምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀፅ 8 መሰረት “የፌደራሉ መንግስት፤ የሀገርና የሕዝብ መከላከያ፣ የደህንነትና የፖሊስ ኃይሎች የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች ሲጥሱና የሀገር ደህንነትን የሚነካ ተግባር ሲፈፅሙ ተከታትሎ ማጣራትና አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ” አልቻልም። በመሆኑም፣ አፈ-ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ለሕገ መንግስቱ፥ ለሕዝቡና ለሕሊናቸው ተገዢ በመሆን ራሳቸውን ከኃላፊነት ከማውረድ በስተቀር ሌላ ምርጫና አማራጭ የላቸውም።

ከዚህ በተጨማሪ፣ ላለፉት አስር አመታት ሕገ መንግስቱ የተደነገጉ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶችን ሙሉ በሙሉ በሚጥሰው የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ አማካኝነት 1405 የሚሆኑ የፖለቲካ መሪዎች፥ ጋዜጠኞች፥ ጦማሪያን፥ የመብት ተሟጋቾች፥ የሃይማኖት መሪዎች፣….ወዘተ ተከሰው በእስር የማቀቁና እየማቀቁ ባለበት ሀገር ለሕገ መንግስቱ ተገዢ መሆን አይቻልም። ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ በተለይ በኦሮሚያ፥ አማራና ደቡብ ክልሎች ዜጎች መብትና ነፃነታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ ብዙ ሺህዎች ለሞት፥ እስራትና የአካል ጉዳት ሲዳረጉ፣ በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 55(16) በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት ይህን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማስቆም የተሳነው ምክር ቤት ተገዢነቱ ለአስፈፃሚው አካል እንጂ ለሕገ መንግስቱ፥ ለሕዝቡ ወይም ለሕሊናው አይደለም። ስለዚህ ሌሎች የምክር ቤት አባላትም ልክ እንደ አፈ-ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ለሕገ መንግስቱ፥ ለሕዝቡ ወይም ለሕሊናቸው ተገዢ በመሆን የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የደህንነትና የፖሊስ ኃይሎች በዜጎች ላይ ከሚፈፅሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የሀገር ደህንነትን ከሚያናጋ ተግባር እንዲቆጠቡ ለማድረግ የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው። Via Dhábasá Wakjira Gemelal


አንድ ጄኔራል የህወሃት አገዛዝን ከድተው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 26/2010) በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በወታደራዊ ደህንነት ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩ አንድ ጄኔራል ስርአቱን ከድተው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ።

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ስርአቱን ከድተው በአሜሪካ የቀሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ጥሩነህ የተባሉ ከፍተኛ መኮንን ናቸው።

ከወር በፊት በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ አዘጋጅነት በዋሽንግተን በተካሄደ ጸረ አይ ሲስ አለም አቀፍ ዘመቻ ላይ ከተገኙ የኢትዮጵያ ልኡካን አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ጥሩነህ በዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራው ልኡካን ቡድን ወደ ሀገር ቤት ሲመለስ እርሳቸው ከቡድኑ ተለይተው ቀርተዋል።

ግሎባል ኮአሊሽን ቱ ዲፊት አይሲስ በተባለውና 72 ሀገራትን በአባልነት ያቀፈው ጥምረት ጉባኤ ላይ ለመገኘት መጥተው ከልኡካኑ ተለይተው የቀሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውንም ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ በወታደራዊ ደህንነት መመሪያ ውስጥ ይሰሩ እንደነበር የተገለጸው ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ነባር የብአዴን ታጋይ ነበሩ።

በመስከረም 2009 የብርጋዴር ጄኔራልነት ማዕረግ ካገኙት መኮንኖች አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ስርአቱን ከድተው መቅረታቸውን ኢሳት አረጋግጧል።

ጄኔራሉ የብአዴን አባል ሆነው ስርአቱን መቀላቀላቸው ታውቋል።

በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛው የአዛዥነት ስፍራ ከ90 በመቶ በላይ በትግራይ ተወላጆች መያዙ ሲገለጽ ቆይቷል።

በዚህ ሰራዊት በተወሰነ ቁጥር ከነበሩት የሌላ ብሔረሰብ ተወላጆች ባለፉት 10 አመታት ከ20 በላይ የኦሮሞና የአማራ ጄኔራሎች ታስረዋል፣ተባረዋል፣ያለዕድሜያቸው በጡረታ የተሸኙ መኖራቸውም ታውቋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ፣ብርጋዴር ጄኔራል ሃይሉ ጎንፋ ስርአቱን ከድተው ከወጡት ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው።

ሜጄር ጄኔራል አለምሸት ደግፌ፣ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌና ብርጋዴር ጄኔራል ኩመራ አስፋው ማዕረጋቸውን ተገፈው ከስርአቱ ተባረዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ በመንግስት ግልበጣ ሙከራ ተፈርዶባቸው በወህኒ ይገኛሉ።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በ2001 ከሰራዊቱ አመራርነት ተይዘው የታሰሩና በግልበጣ ሙከራ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው ናቸው።

ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌና ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰ ደግሞ ከሰራዊቱ በጡረታ ተሸኝተዋል።

ቀደም ሲል በጡረታ ከተሸኙት አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ሃይሌ መለስ ከአመት በፊት ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ታውቋል።

ለተባበሩት መንግስታት 72ኛ ጉባኤ ከአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ወደ ኒዮርክ አቅንተው የነበሩት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሮቶኮል ሃላፊ አቶ ባዬ ታደሰ ስርአቱን በመክዳት አሜሪካ መቅረታቸውን በሳምንቱ መጀመሪያ ለቪኦኤ መግለጻቸው ይታወሳል።

የፕሮቶኮል ሃላፊው በአቶ ሃይለማርያም ከተመራው የኢትዮጵያ ልኡካን ጋር አሜሪካን የገቡት በተያዘው ወር እንደሆነም ታውቋል።

No comments yet.

Leave a Reply

Designed and Developed by NextGen IT Solutions