ከእሬቻ ለአሸንዳ የተፃፈ ደብዳቤ – የሳምንቱ ምርጥ ደብዳቤ!

(ከእሬቻ ለአሸንዳ የተፃፈ ደብዳቤ)

የሳምንቱ ምርጥ ደብዳቤ!

“ከመይ ከመይ፠ አቦይ እንዴት ነህ አሸንዳ? …
አወከኝ ወይ ጓዴ? … ኦቦ እሬቻ ነኝ የኦሮሞው ልጅ የዛ የኣባ ገዳ !
አይተ አሸንዳ ባለፈው ያከበርከው በዓልህ ደመቀ? …
ጥይት ሳይፈነዳ ደም ሳይንቦጫረቅ በደስታ አለቀ? ..
. እንደምነው ጮማው? .. እንዴት ነው ፍሪዳው? ..
እንዴት ነው ኮካዎች? .. ሰላም ነው ሚሪንዳው? …
ዳሽን ቢራ አጀበህ ራያ አጠመቀህ?
ስንት ሚሊየን ብር ለባዕል ተሰጠህ? …
“ፅቡቅ ደሀን ፅቡቅ ጥኡም ደስ ብሎናል ! ..
. በልማታዊ መንግስትህ በጣሙን ኮርተናል!! …

“ቧ ወዲ እሬቻ አንተስ እንዴትነህ?” ስትል ሰማሁ ልበል? …
እኔማ እሬቻን በደስታ ውያለሁ ፤
ከሰላም ወንዝ ወርጄ ደሜን ጠጥቻለሁ ! …
ከቢሾፍቱ ሀይቅ ከሞት በቀር የለም …
አንተ ጋራ ያለው ከኛ ጋር አልመጣም።
የለም ያንተ ውስኪ ! የለም ያንተ ቢራ !
ያንተ ጮማ የለም የለንም ዳንኪራ !! …
ግና ካንተ ጋር የለሌ እኛ ጋር ሞልቶናል .
.. ካንተ ስለሌለ እኛም ደስ ብሎናል!! …
አንተ በርችት ነው ፎቶ ‘ምትነሳ ! ..
. እኛ በጥይት ነው ፎቶ ‘ምንነሳ ! …
አንተ ፈንዲሻ ነው በድስት ‘ምትቆላ …
እኛ በስናይፐር ነው በእሳት ምንቆላ !! ..
. የአንተ ወንዝ ንፁህ ነው ሰላም አጠጥቷል ..
. የኛ ወንዝ ደፍርሷል ክፉኛ ነስሮታል።
አንተ ጨፍረሃል እኛ ኣልቅሰናል
ይሄዉ ነው ታሪኩ ይህንን አይተናል።
ታዲያ ኣቦይ አሸንዳ ኣንተ ስትደንስ እኛስ ምን ይለናል?
ካንተ የተማረንውን ይሀው ጀምረናል
የቀምሰነዉን ቅመስ ፈንጅሻ ይዘናል።
ቆልተ እንዳስተማርከን መቁላት ጀምረናል!
ከፈጣሪ ጋራ በመጪው መስከረም እንደሬቻ ሁሉ ላንተም ይበታናል።

-የግዜ እንጂ የሰዉ ጀግና የለዉም ና መቼም አንረሳዉም!!
መታሰብያነቱ በእሬቻ ላይ ለተሰዉ ሁሉ!

No comments yet.

Leave a Reply

Designed and Developed by NextGen IT Solutions